Monday, December 31, 2018

ለወላጅ አልባ እና እርዳታ ለሚሹ ህፃናት ድጋፍ ተደረገ



በአዲስ አበባ ቤቶች ልማት ፕሮጀክት ጽ/ቤት ከቦሌ ክ/ከተማ ሴቶችና ህፃናት ጉዳዮች ፅ/ቤት ችግረኛ ህፃናትን ለማሳደግና ለማስተማር ለተረከቧቸዉ አምስት ታዳጊ ህፃት የአልባሳትና የትምህረት መርጃ መሳሪያዎች እና ለአዲስ ዓመት የበዓል ማክበሪያ የገንዘብ ድጋፍ አደረጉ፡፡
ዛሬ በኦሮምያ ክልላዊ መንግሰት ፅ/ቤት የስብሰባ አዳራሽ በተደረገ የርክክብ እና የድጋፍ አሰጣጥ ስነ-ስርዓት ላይ ተገኝተዉ ንግግር ያደረጉት አዲሷ የአዲስ አባባ ቤቶች ልማትና አስተዳደር ቢሮ ሃላፊ ኢንጂነር ሰናይት ዳምጠዉ የቤቶች ልማት ፕሮጀክት ፅ/ቤት ሰራተኞችና አመራሮች እያደረጉት ያለዉ ችግረኛ ህፃናትን ተረክቦ የማሳደግ ተግባር በአርአያነት የሚጠቀስ ነዉ ብለዋል፡፡
ኢንጂነር ሰናይት ዳምጠዉ ፕሮጀክት ፅ/ቤቱ ለማሳደግ ለተረከቧቸዉ ህፃናት የተገዛላቸዉን ዩንፎርም፣ጫማ ካለበሱ የመማሪያ ቁሳቁሶቹን፣ ቦርሳዎችን ካስረከቡ በኋላ ባደረጉት ንግግር እንደዚህ አይነት ማህበራዊ መተሳሰብና መረዳዳት ባለበት ተቋም ተመድቤ በመስራቴ ደስተኛ ነኝ በማለት እሳቸዉም የዚህ ዓላማ ተቋዳሽ በመሆን የአንድ ሺህ ብር ድጋፍ አድርገዋል ፡፡
የአዲስ አበባ ቤቶች ልማት ፕሮጀክት ጽ/ቤት ሰራተኞች በራስ ተነሳሽነት በየወሩ ከደመወዛቸዉ እየተቆረጠ ለወገን ደራሽ ወገን ነዉ በሚል መርህ አምሰት ህፃናትን በቋሚነት በየወሩ ለመርዳት እና ለመንከባከብ ሃላፊነት ወስደዉ ህፃናቱን ከተረከቡ በኋላ በዛሬዉ እልት ያደረጉት ገንዘብ እና የቅስቀሳ ድጋፍ እንዳስደሰታቸዉና ድጋፉን ለማጠናከር ህፃናቱ
የተሻለ ኑሮ እንዲኖሩ ለማስቻል የተለያዩ የድጋፍ  ማሰባሰቢያፕሮግራም በመንደፍ በጋራ እንደሚንቀሳቀሱ ቃል ገብተዋል፡፡
አቶ ኃረጎት ዓለሙ ከቢሮ ሀላፊዋ ጋር በመሆን አልባሳቱን ካለበሱ በኋላ ሰራተኛዉ በዝግጅቱ ላይ በፍላጎት ባደረጉት ተጨማሪ የገንዘብ ማሰባሰብ ድጋፍ ለአምስቱ ህፃናት ለአመት በዓል መዋያ ለእያንዳንዳቸዉ 730 ብር አስረክበዋል፡፡
በተጨማሪም ለአንዲት መንታ ህፃናት ይዛ በችግር ለምትኖር እናትም ለበዓል 1ሺህ ብር እንዲሰጣት ካደረጉ በኋላ ይህች ሴት በቋሚነት ከሚረዱት አምስት ህፃናት ጋር ተደምራ እንድትረዳ አቅጣጫ አስቀምጠዋል፡፡
አቶ ኃረጎት ዓለሙ ይሕን በጎ ተግባር በማስተባበርና በመምራት ለደከሙት የኮሚቴ አባላት ላቅ ያለ ምስጋና ካቀረቡ መኋላ ሰራተኛዉ መዋጮዉን አጠናክሮ እንዲቀጥል ማሳሰባቸዉን የዘገበልን የአዲስ አበባ ቤቶች ልማት ፕሮጀክት ጽ/ቤት ኮሚዩንኬሽን ጉዳዮች የስራ ሂደት ነዉ፡፡ሪፖ/ጋ.ተ.