Thursday, January 31, 2019

ዜና በአዲስ አበባ ቤቶች ልማት ፕሮጀክት ፅ/ቤት በመገንባት ላይ ያሉ ቤቶችን አጠናቆ ለተጠቃሚዉ ለማስተላለፍ የክትትልና ድጋፍ ስራዉ ሊጠናከር እንደሚገባ ተገለፀ፡፡ የ2011 የመጀመሪያ 6ወር ቢኤስ ሲ እቅድ አፈፃፀም ምዝና ለማካሄድ በተዘጋጀ ቲኦር ላይ ከየስራ ሂደቱ እና ከቅ/ፕ/ፅ/ቤቱ ለተወጣጡ መዛኝ ባለሙያዎች ኦረንቴሽን ተሰጥቷል፡፡ የክትትል ድጋፍና ምዘና ደጋፊ የስራ ሂደት መሪ አቶ ሰለሞን ንዳ በኦረንቴሽኑ ላይ ባቀረቡት ሰነድ እንደገለፁት ምዘናዉ የሚደረገዉ የማዕከል የስራ ሂደቶች፣ 17 ቅርንጫፍ ፕሮጀክት ፅ/ቤቶችና የአግሮስቶን ፋብሪካ የስራ ክፈሎቹ ከዋና ስራ አስኪያጅ ጋር የተፈራረሙት የ2011 ቢኤስሲ እቅድ መሠረት አድርጎ ነው፡፡ የምዘና ሂደቱ ከጽ/ቤቱ ሠራተኞች በተጨማሪ የአማካሪ ድርጅቶች፣ የሥራ ተቋራጮችና የጥቃቅንና አነስተኛ ተቋማትን እንደሚያካትት ገልፀው 121 ዋና፣ንዑስ እና ደጋፊ ያሥራ ሂደቶች እናዲሁም በማዕከል እና በቅርነጫፍ የሚገኙ 236 ኬዝ ቲሞች በምዘናዉ ዉስጥ እንዲያልፉ ይደረጋል ብለዋል፡፡ ከ2400 በላይ ፈፃሚዎች ተሳታፊ እንደሚሆኑም አክለው ገልፀዋል፡፡ እንደ አቶ ሰለሞን ገለፃ በዋና ስራ አስኪያጅ የሚመራ አብይ ኮሚቴ የተቋቋመ ሲሆን 6 ቡድኖች እንዲቋቋም ተደርጓል፡፡ የምዘና ቡድኖቹም በየሁለት ቀኑ የግንኙነት ጊዜ ተቀምጦላቸው ሥራዎች የሚገመግሙ ይሆናል፡፡ ፕሮጀክት ጽ/ቤቱ በ2011 የቢኤስሲ ዕቅድ መሠረት ታህሳስ ለማጠናቀቅ በእቅድ የተያዙ ቤቶች አፈፃፀም በምን ደረጃ ላይ እንደሚገኝ ከመገምገም በተጨማሪ ሁሉም ፈፃሚዎች በከተማ ደረጃ የተያዘውን አቅጣጫ በመከተል እንደሚመዝኑ ታውቋል፡፡ ይህም ሥራን ቆጥሮ የመስጠትና የመቀበል ባህልን እንደሚያዳብር መሆኑን በውይይቱ ወቅት ተገልጿል፡፡ ጽ/ቤቱ ከ94 ሺህ በላይ የጋራ መኖሪያ ቤቶች እንዲሁም 1717 የኪራይ ቤቶች ግንባታ እያከናወነ እንደሚገኝ ከአዲስ አበባ ቤቶች ልማት ፕሮጀክት ፅ/ቤት የኮሙኒኬሽን ጉ/ደ/የስ/ሂደት የደረሰን ዘገባ ያመለክታል፡፡

Monday, January 21, 2019

የተከበሩ ባለጉዳያችን ትክክለኛዉን የአዲስ አበባ ቤቶች ልማት ፕሮጀክት ፅ/ቤት መረጃ በሚከተሉት አድራሻዎቻችን ማግኘት የሚችሉ መሆኑን እየገለፅን፡፡  የፌስቡክ ገፅ፡- Housing Development Project Office 20/80  የፌስቡክ አካዉንት፡- ቤቶች ኮሙኒኬሽን (የአዲስ አበባ ቤቶች ፕሮጀክት)  ብሎገር፡- ADDIS ABABA HOUSING PROJECT OFFICE  ዩ ቲዩብ፡- Addis Ababa housing Development project office  ቲዉተር፡- Addis Ababa Housing Development Project Office  ወርድ ፕረስ፡- Hdpo communication  የኢ-ሜይል አድራሻ፡- hdpocommunication@gmail.com  ዌብ ሳይት፡- www.http://www.aahdpo.gov.et/  ስልክ ቁጥር የኮሙኒኬሽን፡- 0118787940 በተጨማሪም ከላይ የተገለፀዉን የፈስ ቡክ ገጽ እና አካዉንት በማድረግ ሀሳብ አስተያየቶን ማንሸራሸር ይችላሉ እናመሰግናለን፡፡

Sunday, January 13, 2019

የመጀመሪያዉ መንፈቀ አመት ግምገማ

በመጀመሪያው መንፈቀ ዓመት የሥራ አፈፃፀም ግምገማ ላይ ውይይት ጥር ቀን 2011 ዜና በአዲስ አበባ ቤቶች ልማት ፕሮጀክት ጽ/ቤት ለ2011 በጀት ዓመት በዕቅድ የተያዙ የግንባታ ተግባራትን ለማሳካት የሚያስችል የተከለሰ ዕቅድ ተዘጋጅቶ ተግባራዊ እንቅስቃሴ መጀመሩ ተገለፀ፡፡ የፕሮጀክት ጽ/ቤቱ ባለሙያዎችና አመራሮች በመጀመሪያው መንፈቀ ዓመት የሥራ አፈፃፀም ግምገማ ላይ ውይይት አካሂደዋል፡፡ የፕሮጀክ ጽ/ቤቱ ሠራተኞች ባካሄዱት ውይይት ላይ እንደተገለፀው በ2011 በጀት ዓመት የመጀመሪያው መንፈቀ ዓመት የሥራ ክንውን ላይ የተገኙ መልካም ውጤቶችና ያጋጠሙ ችግሮችን ታሳቢ ያደረገ የተከለሰ ዕቅድ በማዘጋጀት ወደ ተግባር የተገባ ሲሆን ዕቅዱ በቀጣዮቹ ስድስት ወራት የተሻለ ውጤት ለማስመዝገብ ያስችላል ተብሎ ይጠበቃል፡፡ የፕሮጀክት ጽ/ቤቱ ዋና ሥራ አስኪያጅ ኢንጂነር ኪሮስ መሰለ እንዳመለከቱት በተለያዩ ሳይቶች ግንባታቸው እየተፋጠነ ያሉት የጋራ መኖሪያ ቤቶችን ተመዝግበው በመጠባበቅ ላይ ለሚገኙ የህብረተሰብ ክፍሎች ለማድረስ እየተደረገ ያለው ርብርብ የሚበረታታና ይበልጥ ተጠናክሮ ሊቀጥል የሚገባው ነው፡፡ የፕሮጀክት ጽ/ቤቱ የጥናት፣ ዕቅድና በጀት የሥራ ሂደት መሪ አቶ ተዘከር ፀጋዬ በውይይቱ ላይ ባቀረቡት የስድስት ወራት የሥራ አፈፃፀም ሪፖርት በተለይ ግንባታቸው ባለፈው የ2010 በጀት ዓመት የተጀመሩት ከአንድ ሺህ ሰባት መቶ በላይ ለኪራይ የሚቀርቡ ቤቶች በአሁኑ ወቅት ከ91 በመቶ በላይ መድረሳቸው መልካም ተሞክሮ በመሆኑ ወደ ሌሎች ግንባታዎችም ሊስፋፋ እንደሚገባ አመልክተዋል፡፡ ሪፖርቱን ተከትሎ የውይይቱ ተሳታፊዎች በሰነዘሯቸው አስተያየቶችና ጥያቄዎች መንገድ፣ መብራትና ውሃን የመሰሉ የመሠረተ ልማት አቅርቦቶች አለመሟላት እንዲሁም የግንባታ ግብዓት አቅርቦት እጥረትና ሌሎችም ተያያዥ ችግሮች ትኩረት ሊሰጣቸው እንደሚገባ የጠቆሙ ሲሆን ከመድረኩ ምላሽ ተሰጥቶባቿል፡፡ በፕሮጀክት ጽ/ቤቱ ያለው መልካም አስተዳደር በሚፈለገው ደረጃ እንዲሆን የህብረተሰቡን እርካታ መሠረት ያደረገ ፈጣን ምላሽ በመስጠት የተገልጋዮችን እርካታ ለማረጋገጥ ይበልጥ ጠንክሮ መሥራት እንደሚያስፈልግና በየደረጃው የሚገኙ ባለሙያዎችና ኃላፊዎችም ሥራቸውን በባለቤትነት ስሜት ማከናወን እንደሚጠበቅባቸው ተጠቁሟል፡፡ የአዲስ አበባ ቤቶች ልማት ፕሮጀክት ጽ/ቤት በተለያዩ ሳይቶች ከ94 ሺህ በላይ ቤቶች በመገንባት ላይ እንደሚገኝ የፕሮጀክት ጽ/ቤቱ የኮሙኒኬሽን ጉዳዮች ደጋፊ የሥራ ሂደት ዘግቧል፡፡