Friday, May 3, 2019

ሚያዚያ 2011 ዜና በአዲስ አበባ ቤቶች ልማት ፕሮጀክት ጽ/ቤት በተለያዩ ቅርንጫፍ የቤት ልማት ፕሮጀክት ጽ/ቤቶች ላይ ተመድበው የሚሰሩ አማካሪዎች በመሰረት ላይ ያሉትን የ20/80 የጋራ መኖሪያ ቤቶች ግንባታ ለማፋጠን አዳዲስ ሀሳቦችን አመንጪ በመሆንና ችግሮችን እየፈቱ መፍትሄ በማስቀመጥ ለግንባታው መፋጠን የበኩላቸውን ድርሻ እንዲወጡ የአ/አ ቤቶች ልማት ፕሮጀክት ጽ/ቤት ዋና ስራ አስኪያጅ አቶ ኪሮስ መሰለ አሳሰቡ፡፡ በአማካሪዎች ዙሪያ እየታዩ ያሉ ችግሮች(የመፍትሄ አቅጣጫዎች) ለማስቀመጥ በተጠራው የውይይት መድረክ ላይ ዋና ስራ አስኪያጅ አቶ ኪሮስ መሰለ እንደተናገሩት ለመኖሪያ ቤቶች ግንባታ መጓተት የአማካሪው ሚና ከፍተኛ እንደሆነ ጠቅሰው በተለይም ስኬጅዋል እያወጡ ለኮንትራክተሩ መስጠትና በተሰጠው ጊዜ ሰሌዳ ስራውን ባላከናወነ ተቋራጭና ማህበራት ላይ እርምጃ ያለመውሰድ፣ የሳይት ተቆጣጣሪዎችን በበቂ ሁኔታ ያለመመደብ፣ አዳዲስ ሀሳቦችን በማፍለቅ አማካሪው ግንባታ እንዲፋጠን ጥረት ያለማድረግ ከሚታዩ ችግሮች ጥቂቶቹ እንዲሆኑ ጠቅሰዋል፡፡ አቶ ሙሉጌታ ፀሀይ ወርቄ በቤቶች ልማት ፕ/ጽ/ቤት የግንባታ ክትትልና ድጋፍ ም/ስራ አስኪያጅ በሁሉም ቅርንጫፍ ጽ/ቤቶች ባሉ አማካሪ ድርጅቶችና በነሱ ስር ባሉ ባለሞያዎች ዙሪያ እየታዩ ያሉ ችግሮችን በዝርዝር ካስቀመጡ በኋላ የአሁኑ ውይይትም ችግሮቹን ደረጃ በደረጃ በመፍታት ግንባታውን በማፋጠን በጉጉት የሚጠበቀውን ቤት ፈላጊ ችግር መፍታት አስፈላጊ ነው ብለዋል፡፡ አማካሪዎቹ በበኩላቸው የተነሱት ችግሮች መኖራቸውን ተቀብለው ይሁን እንጂ በነሱም በኩል ያሉ ችግሮችን ተቋሙ ፈትሾ ሊፈታላቸው እንደሚገባ ጠቁመዋል ከዚህም አንፃር በተለይም ከክፍያ መዘግየት ጋር በተያያዙ ባለሞያዎች እየለቀቁባቸው ስለመሆኑና የማቴሪያል አቅርቦቶች መጓተት፣ የኤሌክትሪክና የውሀ ችግሮች ትኩረት ሊሰጣቸው የሚገቡና በነዚህ ችግሮች ሳቢያም ለግንባታ መጓተት ምክንያት እየሆነን ነው ብለዋል፡፡ በመጨረሻም ችግሮችን እየፈቱ በመሄድ ቀጣይ ግንባታው በዘገየው ልክ ፈጥኖ መፍትሄ በማስቀመጥ ግንባታን ለማፋጠንና አጠናቆ ለመውጣት የጋራ መግባባት ላይ መድረሱን የፕ/ጽ/ቤቱ ኮሙኒኬሽን ስራ ሂደቱ ዘግቧል፡፡ Image may contain: sky, cloud and outdoor