Thursday, January 31, 2019

ዜና በአዲስ አበባ ቤቶች ልማት ፕሮጀክት ፅ/ቤት በመገንባት ላይ ያሉ ቤቶችን አጠናቆ ለተጠቃሚዉ ለማስተላለፍ የክትትልና ድጋፍ ስራዉ ሊጠናከር እንደሚገባ ተገለፀ፡፡ የ2011 የመጀመሪያ 6ወር ቢኤስ ሲ እቅድ አፈፃፀም ምዝና ለማካሄድ በተዘጋጀ ቲኦር ላይ ከየስራ ሂደቱ እና ከቅ/ፕ/ፅ/ቤቱ ለተወጣጡ መዛኝ ባለሙያዎች ኦረንቴሽን ተሰጥቷል፡፡ የክትትል ድጋፍና ምዘና ደጋፊ የስራ ሂደት መሪ አቶ ሰለሞን ንዳ በኦረንቴሽኑ ላይ ባቀረቡት ሰነድ እንደገለፁት ምዘናዉ የሚደረገዉ የማዕከል የስራ ሂደቶች፣ 17 ቅርንጫፍ ፕሮጀክት ፅ/ቤቶችና የአግሮስቶን ፋብሪካ የስራ ክፈሎቹ ከዋና ስራ አስኪያጅ ጋር የተፈራረሙት የ2011 ቢኤስሲ እቅድ መሠረት አድርጎ ነው፡፡ የምዘና ሂደቱ ከጽ/ቤቱ ሠራተኞች በተጨማሪ የአማካሪ ድርጅቶች፣ የሥራ ተቋራጮችና የጥቃቅንና አነስተኛ ተቋማትን እንደሚያካትት ገልፀው 121 ዋና፣ንዑስ እና ደጋፊ ያሥራ ሂደቶች እናዲሁም በማዕከል እና በቅርነጫፍ የሚገኙ 236 ኬዝ ቲሞች በምዘናዉ ዉስጥ እንዲያልፉ ይደረጋል ብለዋል፡፡ ከ2400 በላይ ፈፃሚዎች ተሳታፊ እንደሚሆኑም አክለው ገልፀዋል፡፡ እንደ አቶ ሰለሞን ገለፃ በዋና ስራ አስኪያጅ የሚመራ አብይ ኮሚቴ የተቋቋመ ሲሆን 6 ቡድኖች እንዲቋቋም ተደርጓል፡፡ የምዘና ቡድኖቹም በየሁለት ቀኑ የግንኙነት ጊዜ ተቀምጦላቸው ሥራዎች የሚገመግሙ ይሆናል፡፡ ፕሮጀክት ጽ/ቤቱ በ2011 የቢኤስሲ ዕቅድ መሠረት ታህሳስ ለማጠናቀቅ በእቅድ የተያዙ ቤቶች አፈፃፀም በምን ደረጃ ላይ እንደሚገኝ ከመገምገም በተጨማሪ ሁሉም ፈፃሚዎች በከተማ ደረጃ የተያዘውን አቅጣጫ በመከተል እንደሚመዝኑ ታውቋል፡፡ ይህም ሥራን ቆጥሮ የመስጠትና የመቀበል ባህልን እንደሚያዳብር መሆኑን በውይይቱ ወቅት ተገልጿል፡፡ ጽ/ቤቱ ከ94 ሺህ በላይ የጋራ መኖሪያ ቤቶች እንዲሁም 1717 የኪራይ ቤቶች ግንባታ እያከናወነ እንደሚገኝ ከአዲስ አበባ ቤቶች ልማት ፕሮጀክት ፅ/ቤት የኮሙኒኬሽን ጉ/ደ/የስ/ሂደት የደረሰን ዘገባ ያመለክታል፡፡

No comments:

Post a Comment